• መንፈሳዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት

                                   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

    በኢ•አ•መ የቅዱስ ሚካኤል ሰራተኛ ጉባኤ  ሁሌ በወር  በቅዱስ ሚካኤል ዕለት ወርሃዊ ጉባኤ ላይ የንስሐ ትምህርት እንደሚሰጥ ይታወቃል እሱ እንዳለ የሃይማኖት ትምህርት  የግድ መማር ይኖርብናል ነገር ግን ሁለቱንም መርሃግብር ለማስኬድ ካለን የስራ ሁኔታ አንጻር በአካል ተገኝቶ ለመማር ስለሚከብድ የሃይማኖት ትምህርቱን ከረጅም ጊዜ  የማስተማር ልምድም በቤተክርስቲያን እውቅና  ካላቸው የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበትን ት/ቤት ጋር በመሆን በስድስት ወር ውስጥ የሚጠናቀቅ የርቀት ትምህርት ነው።

     የምንማራቸው ትምህርቶች

    ሥነ ፍጥረት

    ትምህርተ ሃይማኖት

    ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን

    ሥርዓት ቤተክርስቲያን

    ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው

    ነገረ ማርያም

    ነገረ ቅዱሳን

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በብሉይ ኪዳን

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በሐዲስ ኪዳን

    የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ

    የቤተክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ ናቸው

    ትምህርቱ አጠናቀን በሃይማኖት ውስጥ ኖረን የመንግስቱ ወራሽ እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን !::